1️⃣ Offset Dish (ኦፍሰት ዲሽ)
ይህ በብዙ ቤቶች ላይ የምንገናኝበት የተለመደ የዲሽ አይነት ነው።
በአብዛኛው 60cm እስከ 90cm መጠን ይኖረዋል።
ለKu-band ሳተላይቶች ይጠቅማል።
- ✔ ለመጫን ቀላል የሆነ
- ✔ ዋጋው ዝቅተኛ የሆነ
- ✔ ለቤት ተጠቃሚ ተስማሚ
2️⃣ Prime Focus Dish (ፕራይም ፎከስ ዲሽ)
ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ዲሽ ነው።
ብዙ ጊዜ C-band ለመቀበል ይጠቅማል።
በገጠር አካባቢ ይታያል።
- ✔ ከፍተኛ ሲግናል የቀበላል
- ✔ ለC-band ተስማሚ ነው
- ❗ ትልቅ ቦታ ይፈልጋል መጠኑ ትልቅ ስለሆነ
3️⃣ Motorized Dish (ሞተር ያለው ዲሽ)
ይህ ዲሽ በሞተር የሚንቀሳቀስ ነው።
በአንድ ዲሽ ብዙ ሳተላይቶችን መቀበል ይቻላል።
- ✔ ብዙ ሳተላይት መቀበል ይችላል
- ✔ አውቶማቲክ እንቅስቃሴ ያለው
- ❗ ዋጋው ከፍተኛ ነው